የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቡና ማልጠኛ ማእከል በተለያዩ የቡና ሙያዎች ላይ የሰለጠኑ ተማሪዎችን አስመርቀ፡፡

ግንቦት 05/2018 -ኢ/ቡ/ሻ/ ባለስልጣን

በኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ስር የሚገኘው የቡና ማሰጠኛ ማእከል ለ16ኛ ጊዜ በባሬስታ፣ በቡና ቅምሻ፣ በቡና ግብይትና ዶክመንቴሽን እና እና በቡና መቁላት ሙያዎች 119 ሰልጣኞችን በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አስመርቋል፡፡


በምረቃው ላይ ክቡር ዶክተር አዱኛ ደበላ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር፣ ክቡር አቶ ሻፊ ኡመር የገበያ ልማትና ቁጥጥር ዘርፍ ሃላፊና ምክ/ ዋና ዳይሬክተር፣ ክቡር አቶ ታጋይ ኑሩ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ልማት ዘርፍ ሃላፊና ምክ/ ዋና ዳይሬክተር፣ የዋና ዳ/ር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሰፊሳ አባቡና የዩኒዶ ተወካይ ዶክተር ካሳዬ ቶሌሳ ተገኝተዋል ፡፡
ክቡር ዶክተር አዱኛ በምረቃው መርሃግብር ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ባለስልጣን መ/ቤቱ ከቡና ልማቱ እና ግብይቱ በተጨማሪ በቡና ባለሙያ በኩል ያለውን ክፍተት ለመሙላት ተልኮ ወስዶ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ተመራቂዎች የኢትዮጵያ ቡና አምባሳደሮቻችን ናችሁና በተሰማራችሁበት የሙያ ዘርፍ ሁሉ ቡናችንን በማስተዋወቅ ስኬታማ ስራ እንደምትሰሩ እምነቴ ነው ብለዋል፡፡


ወ/ሮ ፍሬህይወት አሰፋ የማሰልጠኛ ማእከሉ መሪ ስራ አስፈጻሚ በምረቃው መርሃግብር መክፈቻ ላይ በማእከሉ አገልግሎት አሰጣጥና የስልጣኛ አይነቶች በሰጡት ማብራሪያ በቡና ቅምሻ ሙያ ለአስራ ሁለተኛ ዙር 42 ፤ በባሬስታ ሙያ ለአስራ አምስተኛ እና ለአስራ ስድስተኛ ጊዜ 25 ተማሪዎችን፤ ለአራተኛ ዙር ደግሞ በቡና መቁላት ሙያ 28 ተማሪዎችን እንዲሁም በቡና ግብይት ኤክስፖርት ዶክመንቴሽን 24 ተማሪዎችን አሰልጥኖ ለምረቃ አብቅተቷል ብለዋል ፡ ወይዘሮ ፍሬህይወት አያይዘውም ማእከሉ ስልጠና መስጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአራቱም የስልጠና ዘርፎች ሴት 306 እና ወንድ 429 በድምሩ 735 ሰልጣኞችን የሙያ ባለቤት በማድረግ በሚፈልጉት የሙያ ዘርፍ እንዲሰማሩ በማድረግ ተልኮውን በመወጣት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ በዚህ የስልጠና ዙር ማዕከሉ ሁለት አካል ጉዳተኛ ሴቶችን እና አንድ እናት በማሰልጠን ለሴቶች እኩልነት እና የስራ እድል ተጠቃሚነት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡


ማእከሉ ከተለያዩ አለም አቀፍና አገራዊ አጋር ድርጅቶች ከዩኒዶ፤ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ከግብርና ሚኒስቴር እና ሌሎች ማዕከሉን ከሚያግዙ ድርጅቶች ጋር በቅነጅት በመስራት ላይ እንደሆነ ተብራርቷል፡፡ ሰልጣኝ ተመራቂዎች የምስክር ወረቀታቸውን ከክቡር ዶክተር አዱኛ ደበላ እጅ ተቀብለዋል ፡፡
በመጨረሻም በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላሳዩ 7 ሰልጣኝ ተመራቂዎች ልዩ ሽልማት ከዋና ዳይሬክተሩ ተበርክቶላቸዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *